ዋና ገጽ

ሙስሊሞች ከተፅዕኖ ነፃ የሚሆኑት መቸ ነው ?  

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባሳለፏቸው ዘመናት በተፈራረቁባቸውን ነገስታት እና ፈላጭ ቆራጮች መንግስታት ዘግናኝ የጭቆና ጊዚያትን በመቻቻል ሳይሆን በመቻል አሳልፈዋል ። ይሁንና ግፈኛው የደርግ መንግስት ከተወገደ በኃላ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ትግል ወደ ስልጣን የመጣው የኢህአዴግ መንግስት ጭቆናውን በማጠንከር እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ሁሉ በመናቅ እና በማዋረድ (አሕባሽ) የተሰኘ ጠማማ አስተሳሰብ እስልምና ውስጥ ለማስገባት እና ከሒወታችን በላይ የምናፈቅረውን እስልምናችንን በመዳፈር ዘመን የማይሽረው እና ከያንዳንዱ ሙስሊም ህሊና በጭራሽ የማይፋቅ ጠባሳን በመትከል ኢትዮጵያን ወደ አለመረጋጋት የሚያመራትን የሽብር መንገድ በመቀየስ ለኢትዮጵያውያን ሞትን ሊያጎርስ ሽር ጉዱን ይዟል ። አሏሁ አክበር !!!

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ግን በሃያሉ አሏህ ሁሌም ይመካሉ !!! 

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የነፃነት ጥያቄ በኢህአዴግ ጭቆና በጭራሽ አይዳፈንም !!!

ሙስሊሞች ከተፅኖ ነፃ የሚሆኑት መቸ ነው ? ክ1


ሙስሊሞች ከተፅኖ ነፃ የሚሆኑት መቸ ነው ? ክ2

 


No comments:

Post a Comment